1.2 KiB
1.2 KiB
ጢሞቴዎስ
ጢሞቴዎስ እርሱ በነበረበት ልስጥራ ከተማ ጳውሎስ ባገለገለ ጊዜ በክርስቶስ ያመነ ወጣት ሰው ነበር። በኋላም ጳውሎስ ባደረገው በርካታ ሐዋርያዊ ጉዞ አብሮት ነበር፤ የአዲስ አማኞች ማኅበረ ሰብ መጋቢ በመሆንም አገልግሏል።
- አያቱ ሎይድና እናቱ አውንቅ በክርስቶስ ያመኑ አይሁዳውያን ቢሆኑም፣ አባቱ ግሪካዊ ነበር።
- ጢሞቴዎስ በግማሽ ጎኑ አይሁዳዊ ስለ ነበር እነርሱን ቅር ሲያሰኝ ከአይሁድ ጋር ተገናኝቶ እንዲያገልግላቸው ጳውሎስ ገረዘው።
- ጳውሎስና የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች እጃቸውን በመጫንና በጸሎት ወግ ባለው ሁኔታ ጢሞቴዎስን ሾሙት።
- አዲስ ኪዳን ውስጥያሉትን አንደኛና ሁለተኛ የጢሞቴዎስ መልእክቶች ጳውሎስ የጻፈው የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ወጣት መሪ ለነበረው ጢሞቴዎስ መመሪያ ለመስጠት ነበር።