1.1 KiB
1.1 KiB
ሴሎ
ሴሎ በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን አሸንፈው የያዟት በግንብ የተከበበች የከነዓናውያን ከተማ ነበረች
- የሴሎ ከተማ የሚገኘው ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምዕራብና ከቤቴል ከተማ ሰሜን ምሥራቅ ነበር
- ኢያሱ እስራኤልን እየመራ በነበረ ዘመን የሴሎ ከተማ የእስራኤላውያን መሰብሰቢያ ነበረች
- ከምድረ ከነዓን ለእያንዳንዳቸው የሚሰጠውን ርስት ድርሻ ከኢያሱ ለመስማት አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች በሴሎ ተሰብስበው ነበር
- በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ከመሠራቱ በፊት እስራኤላውይን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ ወደሴሎ ይመጡ ነበር
- ሳሙኤል ሕፃን እያለ እርሱን ለጌታ ለመስጠት እናቱ ሐና ወደሴሎ ወስዳው ነበር። እግዚአብሔርን ስለማገልገል እየተማረ እዚያ ከካህኑ ከዔሊ ጋር ቆየ