1.4 KiB
1.4 KiB
ሰማርያ፣ሳምራዊ
ሰማርያ ለእስራኤል ሰሜናዊ አካባቢ ላለው ከተማና አካባቢው የተሰጠ ስም ነው። ይህ አካባቢ በምዕራብ በሳሮን ሜዳማ ቦታና በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ይገኛል
- ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሰሜናዊ እስራኤል መንግሥት ዋና ከተማ ነበር። በኋላ ላይ ዙሪያውን ያለው አካባቢም ሰማርያ ተባለ
- አሦራውያን ሰሜናዊውን የእስራኤል መንግሥት ባሸነፉ ጊዜ እዚያ የነበሩ እስራኤላውያን ወደ ተለያዩ የአሦር ከተማ ወሰዷቸው።
- አሦራውያን ብዙ የባዕድ አገር ሰዎች ወደሰማርያ በማምጣት ከዚያ የተወሰዱ እስራኤላውያን ቦታ ላይ አሰፈሯቸው
- አንዳንድ እስራኤላውያን ከእነዚያ ከባዕድ አገር ከመጡ ሰዎች ጋር ተጋቡ፤ ከእነርሱ የተወለዱት ሳምራውያን ተባሉ
- ከፊል አይሁድ በመሆናቸውና የአረማውያን አማልክትን ያመልኩ ስለነበር አይሁድ ሳምራውያንን ይንቋቸው ነበር
- አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ሰማርያ በሰሜን ከገሊላ ጋር፣ በደቡብ ከይሁዳ ጋር ይዋሰን ነበር