986 B
986 B
ፊልጶስ (ሐዋርያው)
ሐዋርያው ፊልጶስ ከመጀመሪያዎቹ አሥራ ሁለት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነበር።
- ፊልጶስ የመጣው ከቤተ ሳይዳ ሲሆን፣ ናትናኤልን ከኢየሱስ ጋር ያስተዋወቀውም እርሱ ነበር።
- አንድ ቀን ከ5000 በላይ ለሆኑ ሰዎች የሚበቃ ምግብ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ኢየሱስ ፊልጶስን ጠይቆት ነበር።
- ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን እራት እየበላ በነበረ ጊዜ ስለ አባቱ እግዚአብሔር ነግሯቸው ነበር። እግዚአብሔር አብን እንዲያሳያቸው ፊልጶስ ኢየሱስን ጠየቀው።
- ይኸኛው ፊልጶስ ከወንጌላዊው ፊልጶስ ጋር እንዳይምታታ ለማድረግ አንዳንድ ቋንቋዎች የሚጠቀሙበት ዘዴ ይኖራቸው ይሆናል።