1.0 KiB
1.0 KiB
ፊልጶስ (ወንጌላዊው)
በኢየሩሳሌም በነበረችው የጥንት ቤተ ክርስቲያን ፊልጶስ ለድኾችና ችግረኛ ክርስቲያኖች በተለይም ለመበለቶች ጥንቃቄ እንዳይደርጉ ከተመረጡ ሰባት መሪዎች አንዱ ፊልጶስ ነበር።
- ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ላገኘው ኢትዮጵያዊ ጨምሮ በይሁዳና በገሊላ አውራጃዎች ውስጥ ለነበሩ ብዙ ከተማ ሰዎች ወንጌልን እንዲያዳርስ እግዚአብሔር በፊልጶስ ተጠቅሟል።
- ከዓመታት በኋላ ፊልጶስ በቂሣርያ እየኖረ ሳለ ጳውሎስና ጓደኞቹ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ ያረፉት እርሱ ቤት ውስጥ ነበር።
- ወንጌላዊው ፊልጶስ የኢየሱስ ሐዋርያ ከነበረው ፊልጶስ የተለየ ሰው እንደ ነበር አብዛኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ይስማማሉ።