957 B
957 B
ፋርስ፣ ፋርሳውያን
ፋርስ በ550 ዓቅክ ታላቁ ቂሮስ የመሠረተው መንግሥት ነው። ማዕከሉ የነበረው የአሁኗ ዘመን ኢራን ያለችበት ቦታ ላይ ነበር። የፋርስ ነዋሪዎች፣ “ፋርሳውያን” ይባላሉ።
- የፋርስ መንግሥት በጣም ሰፊና ኀያል ነበሩ።
- በንጉሥ ቂሮስ ትእዛዝ አይሁድ ከባቢሎን ምርኮ ነጻ ሆኑ፤ የፋርስ መንግሥት ባደረገው እገዛ የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እንደ ገና ተሠራ።
- ዕዝራና ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንደ ገና ለመሥራት ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ የፋርስ መንግሥትን እየገዛ የነበረው ንጉሥ አርጤክስስ ነበር።
- ንጉሥ አርጤክስስን በማግባቷ አስቴር የፋርስ መንግሥት ልዕልት ሆነች።