am_tw/bible/names/michael.md

922 B
Raw Blame History

ሚካኤል

ሚካኤል ቅዱሳንና ታዛዦች ከሆኑት የእግዚአብሔር መላእክት ዋናው ነው። የእግዚአብሔር፣ “ሊቀ መልአክ” ተብሎ የተጠራ እርሱ ብቻ ነው።

  • “ሊቀ መልአክ” “ዋና መልአክ” ወይም፣ “ገዢ መልአክ” ማለት ነው።
  • እስራኤላውያንን በፋርስ ሰራውቲ ላይ የመራ ሚካኤል ነበር፤ በዳንኤል በተነገረው መሠረት በመጨረሻው ዘመን ከክፋት ኀይሎች ጋር በሚደረገው ውጊያ የእስራኤልን ሰራዊት የሚመራም እርሱ ነው።
  • የእግዚአብሔርን ሕዝብ በተመለከተም በእግዚአብሔር ፊት እንደሚማልድ የተነገረበ ሁኔታም አለ።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የተጠሩ አንዳንድ ሰዎች አሉ።