ልስጥራ
ልስጥራ በአንዱ ሐዋርያዊ ጕዞው ጳውሎስ የጎበኛት ታናሽ እስያ ውስጥ የነበረች ከተማ ስም ነው። የምትገኘው የአሁንዋ ቱርክ ባለችበት ሊቃኦንያ አካባቢ ነበር።
- ወንጌላዊና ቤተ ክርስቲያን መሥራች ከሆነው ከጢሞቴዎስ ጋር ጳውሎስ የተገናኘው ወደ ልስጥራ በሄደ ጊዜ ነበር።
- ጳውሎስ አንካሳውን ሰው ከፈወሰ በኋላ በልስጥራ የነበሩ ሰዎች ጳውሎስና በርናባስን ለማምለክ ሞክረው ነበር፤ ሐዋርያቱ ግን ያንን እንዳያደርጉ አጥብቀው ተቃወሙ።