ሉቃስ
ሉቃስ አዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ ሁለት መጻሕፍት የሉቃስ ወንጌልና የሐዋርያት ሥራ ጸሐፊ ነው።
- ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው መልእክት ሉቃስ ሐኪም እንደ ነበር ጳውሎስ አመልክቷል። በሌሎች ሁለት መልእክቶቹም ጳውሎስ ሉቃስን ጠቅሷል።
- ሉቃስ በሁለት ሐዋርያዊ ጉዞዎቹ ከጳውሎስ ጋር አብሮ ነበር፣ በሥራውም ረድቶታል።
- አንዳንድ የጥንት ቤተ ክርስቲያን ጽሑፎች ሉቃስ የተወለደው በሶርያ ባለችው አንጾኪያ ከተማ እንደ ነበር ያመለክታሉ።