1.0 KiB
1.0 KiB
አስቆሮቱ ይሁዳ
የአስቆሮቱ ይሁዳ ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ ነበር። ለአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠ እርሱ ነበር።
- “አስቆሮቱ” የሚለው ፣ ይሁዳ ያደገበትን ከተማ ለማመልከት “ከቂርያት የመጣ” ማለት ሊሆን ይችላል።
- ይሁዳ ሌባ ነበር፤ የሐዋርያቱ ገንዘብ ያዥ በነበረ ጊዜ ከገንዘቡ ጥቂቱን ለራሱ ጥቅም ይሰርቅ ነበር።
- ኢየሱስ የሚገኝበትን ቦታ ለሃይማኖት መሪዎቹ በመንገር ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ ሰጠ።
- የሃይማኖት መሪዎቹ ኢየሱስ ላይ ሞት በፈረዱ ጊዜ፣ ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ በመስጠቱ ተጸጸተ፤ ስለዚህም ራሱን ገደለ።
- መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የኢየሱስን ወንድምና ከደቀመዛሙርቱ አንዱን የመሳሰሉ ይሁዳ የሚባሉ ሰዎች ነበሩ።