1.1 KiB
1.1 KiB
ኢዮስያስ
ኢዮስያስ ለሰላሳ እንደ ዓመት የይሁዳን መግሥት የገዛ እግዚአብሔርን የሚፈራ ንጉሥ ነበር። ሕዝቡ በንስሐ እንዲመለሱና ያህዌን እንዲያመልኩ ለማበረታታት ብዙ ነገሮች አድርጓል።
- አባቱ ንጉሥ አሞን ከተገደለ በኋላ ኢዮስያስ በስምንት ዓመቱ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ።
- በአሥራ ስምንተኛው የአገዛዝ ዘመኑ ንጉሥ ኢዮስያስ የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ እንደገና እንዲሠራ ሊቀካህኑ ኬልቅያስን አዘዘ። ይህ እየተደረገ እያለ የሕጉ መጻሕፍት ተገኙ።
- የሕጉ መጻሕፍት ሲነበቡለት ሕዝቡ ምን ያህል በእግዚአብሔር ላይ እያመፁ መሆናቸውን በማሰብ ኢዮስያስ በጣም አዘነ። የጣዖት አመልኮ ቦታዎች ሁሉ እንዲፈርሱና የጣዖቶች ካህናትም እንዲገደሉ አዘዘ።
- እንደገና የፋሲካ በዓል ማክበር እንዲጀምሩ ሕዝቡን አዘዘ።