1.3 KiB
1.3 KiB
ኢዮአስ
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢዮአስ ተብለው የሚጠሩ ጥቂት ሰዎች ነበሩ።
- አንደኛው ኢዮአስ የእስራኤላዊው ጦረኛ የጌዴዎን አባት ነበር።
- ኢዮአስ ተብሎ የሚጠራው ሌላው ሰው የያዕቆብ ታናሽ ልጅ የብንያም ዘር ነበር።
- በጣም ታዋቂው ኢዮአስ በሰባት ዓመቱ የይሁዳ ንጉሥ የሆነው ነው። በግድያ ሕይወቱን ያጣው የይሁዳ ንጉሥ የአካዝያስ ልጅ ነበር።
- በጣም ትንሽ ልጅ ስለነበር ንጉሥ ለመባል ብቁ እስኪሆን ድረስ የኢዮአስ አክስት ደብቃ ከመገደል አዳነችው።
- በአገዛዝ ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ንጉሥ ኢዮአስ ለእግዚአብሔር እየታዘዘ ነበር። በኋላ ግን ለእግዚአብሔር አልታዘዘም፤ እስራኤላውያንም እንደገና ጣዖቶችን መምልክ ጀምሩ።
- በጦርነት ከቆሰለ በኋላ ንጉሥ ኢዮአስ በሁለት የገዛ ራሱ ባለ ሥልጣኖች ተገደለ።
- ማስታወሻ፣ ይህ ንጉሥ በዚሁ ዘመን እስራኤልን ከግዛው ንጉሥ ኢዮአስ የተለየ ነው።