955 B
955 B
ኢይዝራኤል
ኢይዝራኤል ከጨው ባሕር ደቡብ ምዕራብ ነገድ ክልል ውስጥ የነበረች በጣም ጠቃሚ የእስራኤል ከተማ ስም ነው። ጥቂት የእስራኤል ንጉሦች ቤተመንግሥታቸውን የሠሩት እዚያ ነበር።
- የኢይዝራኤል ከተማ የመጊዶ ሜዳማ ቦታ ምዕራባዊ ጫፎች ከሆኑት አንዷ ስትሆን የኢይዝራኤል ሸለቆ ተብሎም ይጠራል።
- የናቡቴ ወይን እርሻ የነበረው በኢይዝራኤል አክዓብ ቤተመንግሥት አጠገብ ነበር። ነብዩ ኤልያስ እዚያ በነበረው አክዓብ ላይ ትንቢት ተናገረ።
- ክፉዋ የአክዓብ ሚስት ኤልዛቤል የተገደለችው በኢይዝራኤል ነበር።
- ጥቂት ጦርነቶችን ጨምሮ በዚህ ከተማ ሌሎችም ሁነኛ ጉዳዮች ተፈጽመዋል።