1003 B
1003 B
ይስሐቅ
ምንም እንኳ በጣም ያረጁ ቢሆኑም ለእነርሱ እንደሚሰጣቸው እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለሣራ ቃል የገባላቸው ልጅ ነው።
- ከአብርሃም ጋር ያደረገው ኪዳን ይስሐቅንና ዘሮችንም ለዘላለም የሚያካትት እንደ ሆነ እግዚአብሔር ቃል ገብቷል።
- ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ ለእርሱ እንዲያቀርብለት በመንገር እግዚአብሔር የአብርሃምን እምነት ፈተነ።
- የይስሐቅ ልጅ ያዕቆብ አሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት። በኋላ ላይ ዘሮቻቸው አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ሆኑ።
- ይስሐቅ፣ “ሳቀ” ማለት ነው። እርሱና ሣራ ወንድ ልጅ እንደሚወልዱ እግዚአብሔር ለአብርሃም በነገረው ጊዜ ሁለቱም በጣም አርጅተው ስለ ነበር አብርሃም ሳቀ።