927 B
927 B
ሆሴዕ
ሆሴዕ ከክርስቶስ 750 ዓመት በፊት የእስራኤል ነቢይ ነበር።
- የአገልግሎት ዘመኑ ኢየሮብዓምን፣ ዘካርያስን፣ ዖዝያንን፣ አዮአታምንና ሕዝቅያስን በመሳሰሉ የእስራኤልና የይሁዳ ነገሥታት ንጉሥነት ዘመን የዘለቀ በጣም ብዙ ዓመት ነበር።
- ጎሜር የምትባል አመንዝራ ሴት እንዲያገባና ለእርሱ ታማኝ ባትሆን እንኳ እርስዋን መወደዱን እንዳያቋርጥ እግዚአብሔር ለሆሴዕ ተናገረ።
- ይህ ለእርሱ ታማኝ ያልሆነውን ሕዝቡን ማለትም እስራኤልን እግዚአብሔር የመውደዱ ምሳሌ ነበር።
- ሆሴዕ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ትንቢት ተናገር፤ ጣዖቶችን ማምለክ እንዲተዉ አስጠነቀቃቸው።