ኬልቅያስ
ኬልቅያስ በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን የነበረ ሊቀ ካህን ስም ነው።
- ቤተ መቅደስ በሚታደስበት ጊዜ ሊቀ ካህኑ ኬልቅያስ የሕጉን መጽሐፍ አገኘ፤ መጽሐፉ ወደ ንጉሥ ኢዮስያስ እንዲወስድም አዘዘ።
- የሕጉ መጽሐፍ በተነበበ ጊዜ ኢዮስያስ በጣም ተነካ፤ ሕዝቡ እንደ ገና ያህዌን እንዲያመልኩና ለሕጎቹም እንዲታዘዙ አደረገ።
- ኬልቅያስ የተባለው ሌላው ሰው የአልያቂም ልጅ ሲሆን፣ በንጉሥ ሕዝቅያስ ዘመን ቤተ መንግሥት ውስጥ ይሠራ ነበር።