ዕንባቆም
ዕንባቆም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት የነበረ የብሉይ ኪዳን ነቢይ ነው።
- ነቢዩ ትንቢተ ዕንባቆምን የጻፈው በ600 ዓቅክ ኢየሩሳሌም በባቢሎናውያን ከመያዝዋ በፊት ነበር።
- ዕንባቆም በአብዛኛው ትንቢት የተናገረው ከለዳውያንን (ባቢሎናውያንን) አስመልክቶ ሲሆኑ፣ ከነቢዩ ኤርምያስ ቀደ ባሉት ዓመታት ጋር በአንድ ዘመን የነበረ ሰው ነው።
- በጣም ታዋቂ ከሆነው የዕንባቆም ቃሎች አንዱ፣ “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” የሚለው ነው።