1.1 KiB
1.1 KiB
ጌልጌላ
ጌልጌላ ከኢያሪኮ በስተ ሰሜን ያለች አገር ስትሆን፣ ወደ ከነዓን ለመግባት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ወንዝ ከተሻገሩ በኋላ የሰፈሩባት የመጀመሪያ ቦታ ናት።
- እነርሱ ከተሻገሩት የዮርዳኖስ ወንዝ ደረቅ ምድር የወሰዳቸውን አሥራ ሁለት ድንጋዮች ኢያሱ የተከለው በጌልጌላ ነበር።
- ኤልያስ ወደ ሰማይ በሚወሰድበት ጊዜ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ሲሄዱ ኤልያስና ኤልሳዕ ተነሣሥተው የሄዱት ከጌልጌላ ነበር።
- ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “ጌልጌላ” ተብለው የተጠሩ ሌሎች ጥቂት ቦታዎች ነበር።
- “ጌልጌላ” ማለት፣ “የድንግይ ክብ” ማለት ነው። እንዲህ የተባለው እዚያ ተሠርቶ በነበረው ክብ ቅርጽ በነበረው መሠዊያ የተነሣ ሊሆን ይችላል። ከሚሽከረከር ነገር የተያያዘ ነገርን የሚያመለክትም ቃል ነው።