798 B
798 B
ኤፍሬም
ኤፍሬም የዮሴፍ ሁለተኛ ልጅ ነው። የእርሱ ዘር የሆኑት ኤፍሬማውያን አስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ከተሰባሰቡባቸው አንዱ ሆኗል።
- የኤፍሬም ነገድ ከእስራኤል በስተሰሜን ክፍል ከነበሩ አሥሩ ነገዶች አንዱ ነበር።
- መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዳንዴ ኤፍሬም ሰሜናዊውን የእስራኤል መንግሥት በሙሉ ያመለክታል።
- ኤፍሬም፣ “ከተራራማው የኤፍሬም አገር” ወይም፣ “የኤፍሬም ተራሮች” የሚለውን ማጣቀሻ መሠረት በማድረግ ኤፍሬም ተራራማ ወይም ኮረብታማ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ይቻላል።