1.1 KiB
1.1 KiB
ኤልያስ
ኤልያስ በጣም ታዋቅ ከሆኑት የያህዌ ነቢያት አንዱ ነበር። ንጉሥ አክዓብን ጨምሮ ኤልያስ በተለያዩ የእስራኤል ወይም የይሁዳ ነገሥታት ዘመን ነበር ያገለገለው።
- የሞተውን ልጅ ማስነሣትን ጨምር እግዚአብሔር በኤልያስ በኩል ብዙ ተአምራት አድርጓል።
- በአል የተሰኘውን ጣዖት በማምለኩ ኤልያስ ንጉሥ አክዓብን ገሥጾታል።
- እውነተኛው አምላክ ያህዌ ብቻ መሆኑን ለማሳየት ባቀረበው ፈተና ያህዌ የበአል ነቢያትን ተገዳደረ።
- የኤልያስ ሕይወት ማብቂያ ላይ ገና በሕይወት እያለ በተአምር እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ወሰደው።
- ከመቶ ዓመታት በኋላ ኤልያስ ከሙሴ ጋር፣ ተራራው ላይ ከኢየሱስ ጋር ታየ፤ ወደ ፊት ስለሚሆነው የኢየሱስ መከራና በኢየሩሳሌም ስለ መሞቱ እየተነጋገሩ ነበር።