1.3 KiB
1.3 KiB
ቀርሜሎስ፣ የቀርሜሎስ ተራራ
“የቀርሜሎስ ተራራ” በሜዲትራንያን ባሕር አካባቢ ከሳሮን ሜዳማ ቦታ በስተ ሰሜን የነበረውን የተራራ ተረተር ያመለክታል። በጣም ትልቁ ጫፍ 546 ሜትር ከፍታ አለው።
- ከጨው ባሕር ደቡብ በይሁዳ ምድር የሚገኝ “ቀርሜሎስ” የሚባል ከተማ ወይም መንደርም አለ።
- ናባል የሚባለው ሀብታም ባለ ርስትና ሚስቱ አቢግያ ዳዊትና አብረውት የነበሩ የናባል በጎችን ይሸልቱ ለነበሩ ሰዎች ጠባቂ በነበሩበት ቀርሜሎስ በሚባለው መንደር ውስጥ ይኖሩ ነበር።
- እውነተኛው አምላክ ያህዌ ብቻ መሆኑን ለማሳየት ኤልያስ ከባኣል ነቢያት ጋር ፉክክር የገጠመው ቀርሜሎስ ተራራ ላይ ነበር።
- ይህ አንድ ተራራ ብቻ እንዳልነበረ ግልጽ ለማድረግ፣ “የቀርሜሎስ ተራራ” የሚለውን፣ “በቀርሜሎስ ተራሮች ተረተር ላይ የነበረ ተራራ” ወይም፣ “የቀርሜሎስ ተራራ ተረተር” በማለት መተርጎም ይቻላል።