ቤተልሔም ኤፍራታ
ቤተልሔም ኢየሩሳሌም ከተማ አጠገብ የምትገኝ አንዲት ትንሽ የእስራኤል ከተማ ነበረች። “ኤፍራታ” በመባልም ትታወቃለች፤ ምናልባት የመጀመሪያ ስሟ ይህ ሳይሆን አይቀርም
- ንጉሥ ዳዊት የተወለደው እዚያ ስለነበር፥ ቤተልሔም፥ “የዳዊት ከተማ” ተብላለች
- መሲሁ ከ “ቤተልሔም ኤፍራታ” እንደሚመጣ ነብዩ ሚክያስ ተናግሮ ነበር
- በዚያ ትንቢት ፍጻሜ ከብዙ ዓመቶች በኋላ ኢየሱስ በቤተልሔም ተወለደ
- ቤተልሔም፥ “የእንጀራ ቤት” ወይም፥ “የምግብ ቤት” ማለት ነው