1.0 KiB
1.0 KiB
ባሳን
ባሳን ከገሊላ ባሕር በስተምስራቅ አካባቢ ያለ ቦታ ነው። በአሁኑ ዘመን የሶርያ አካል የሆነውን አካባቢና የጎላን ኮረብታን ይሸፍናል
- በብሉይ ኪዳን የነበረው፥ “ጎላን” የሚባለው መጠለያ(መማፀኛ) ከተማ የሚገኘው በባሳን አካባቢ ነበር
- ባሳን በዋርካ ዛፎችና በግጦሽ ሜዳዎቹ የሚታወቅ በጣም ለም አካባቢ ነበር
- ባሳን በአንዳንድ ነገሥታትና በሕዝቦቻቸው መካከል ውጊያ ተደርጎ የነበረበት ቦታ እንደነበር ዘፍጥረት 14 ላይ ተጠቅሷል
- ከግብፅ ከወጡ በኋላ እስራኤል በበረሃ ይንከራተቱ በነበረ ጊዜ እስራኤላውያን የተወሰነውን የባሳን አካባቢ ይዘው ነበር
- ከዓመታት በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ከዚያ አካባቢ የሚያስፈልገውን ነገር ያገኝ ነበር