1023 B
1023 B
አሜስያስ
አባቱ ንጉሥ አዩአስ ከተገደለ በኋላ አሜስያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ።
- ንጉሥ አሜስያስ ከ796-767 ዓቅክ ለሃያ ዘጠኝ ዓመት ይሁዳን ገዛ።
- መልካም ንጉሥ ቢሆንም ጣዖቶች ይመለክበት የነበረውን ከፍታ ቦታዎች ግን አላጠፋም
- የኃላ ኃላ አሜስያስ የአባቱ ገዳዮችን ሁሉ ገደለ
- ዐምፀኞች ኤደማውያንን ድል በማድረግ እንደገና በይሁዳ መንግሥት ቁጥጥር ሥር እንዲሆኑ አደረገ።
- ከእስራኤል ንጉሥ ከኢዮአስ ጋር ውጊያ ቢያደርግም ተሸነፈ የተወሰነው የኢያሩሳሌም ቅጥር ፈርሶ ሳለ ነብር። ከቤተ መቅደሱ የብርና የወርቅ ዕቃዎች ተዘረፉ።
- ከዓመታት በኋላ ንጉሥ አሜሶያስ ፊቱን ከያህዌ አዞረ በኢያሩሳሌም እርሱ ላይ ያሤሩ ሰዎች ገደሉት።