am_tw/bible/kt/save.md

880 B

ማዳን፣ ደኅንነት

“ማዳን” አንድን ሰው ከአንዳች መጥፎ ወይም ጎጂ ነገር መጠበቅ ማለት ነው “ደኅንነት” ከጉዳት ወይም ከአደጋ የተጠበቀ ማለት ነው

  • ቁሳዊ በሆነ ደረጃ ሰዎች ከጉዳት፣ ከአደጋ ወይም ከሞት መዳን ወይም ማምለጥ ይችላሉ
  • በመንፈሳዊ ደረጃ፣ አንድ ሰው፣ “ድኗል” ከተባለ በኢየሱስ መስቀል ላይ ሞት እግዚአብሔር ይቅር ብሎታል፤ በኅጢአቱ ገሃነም ውስጥ ከመቀጣት እንዲያመልጥ ረድቶታል ማለት ነው
  • ሰዎች ከአደጋ መዳን ወይም ማምለጥ ይችላሉ፤ በኅጢአታቸው ምክንያት ለዘላለም ከመቀጣት ሰዎችን የሚያድን ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው