am_tw/bible/kt/sanctuary.md

873 B

ቅዱስ ቦታ

“ቅዱስ ቦታ” ቃል በቃል እግዚአብሔር የሚቀደስበትና የሚመለክበት የተለይ ቦታ ማለት ነው። ከለላና ደኅንነት የሚገኝበትንም ቦታ ሊያመለክት ይችላል

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “ቅዱስ ቦታ” የሚለው ሐረግ አብዛኛውን ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው፣ “ቅድስት” እና፣ “ቅድስተ ቅዱሳን” ይገኙበት የነበረውን መገናኛ ድንኳን ወይም የቤተ መቅደሱን ሕንፃ ለማመልከት ነበር
  • ቅዱሱን ቦታ እግዚአብሔር በሕዝቡ በእስራኤል ማካከል የሚኖርበት ቦታ ብሎታል
  • ራሱንም፣ “ቅዱስ ቦታ” ወይም ሕዝቡ ከለላና ደኅንነት የሚያገኙበት ቦታ በማለት ጠርቷል