1.4 KiB
1.4 KiB
ነቢይ፣ ትንቢት፣ ትንቢት ተናገረ፣ ተመልካች፣ ነቢዪት
“ነቢይ” የእግዚአብሔርን መልእክት ለሰዎች የሚናገር ሰው ነው። ይህን የምታደርግ ሴት ነቢዪት ትባላለች።
- ነቢይ የሚለው የቀድሞ መጠሪያ፣ “ተመልካች” ሲሆን፣ “የሚያይ፣ የሚመለከት ሰው” ማለት ነው።
- ይሁን እንጂ “ተመልካች” የሚለው ቃል አንዳንዴ ሟርተኛን ወይም ሐሰተኛ ነቢይንም ያመለክታል።
- ምንጊዜም ነቢያት ሰዎች በኀጢአታቸው እንዲመለሱና ለእግዚአብሔር እንዲታዘዙ ያስጠነቅቃሉ።
- “ትንቢት” ነቢዩ የሚናገረው መልእክት ነው። “ትንቢት መናገር” የእግዚአብሔርን መልእክት መናገር ማለት ነው።
- ብዙውን ጊዜ የትንቢት መልእክት ወደ ፊት የሚሆነውን ያመለክታል።
- ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ብዙ ትንቢቶች ተፈጽመዋል።
- “ሐሰተኛ ነቢይ” በአልን ከመሳሰሉ ሐሰተኛ አማልክት ተቀብያለሁ የሚለውን መልእክት የሚናገር ወይም የእግዚአብሔር መልእክት እንደ ተቀበለ በውሸት የሚናገር ሰው ነው።