am_tw/bible/kt/love.md

2.7 KiB

ፍቅር

አንድን ሰው መውደድ ለዚያ ሰው ማሰብና መጠንቀቅ እንዲሁም ለእርሱ የሚጠቅመውን ነገር ማድረግ ነው። “ፍቅር” የተለያዩ ትርጕሞች አሉት፤ አንዳንድ ቋንቋዎች በተለያዩ ቃሎች ይገልጹታል። 1. ከእግዚአብሔር የሚመጣው ፍቅር ምንም እንኳ ራስን የሚጠቅም ባይሆንም ሌሎችን መጥቀም ላይ ያተኩራል። ምንም ያድርጉ ምን ይህ ፍቅር ለሌሎች ያስባል፣ ለሌሎች ይጠነቃቃል። እግዚአብሔር ራሱ ፍቅር ነው፤ የእውነተኛ ፍቅር ምንጭም እርሱ ነው።

  • እኛን ከኀጢአትና ከሞት ለማዳን ሕይወቱን መሥዋዕት በማድረግ ኢየሱስ ያሳየው ይህ ዐይነቱን ፍቅር ነበር። መሥዋዕት እስከ መሆን ድረስ ሌሎቹን መውደድ እንዳለባቸው ለተከታዮቹ አስተምሯል።
  • በዚህ ዐይነቱ ፍቅር ሰዎች ሌሎቹን ሲወዱ የሌሎችን ማደግና መሻሻልንም መወደዳቸውን የሚያሳይ ተግባርም ያደራሉ። ሌሎችን ይቅር የሚል ልብም ይኖራቸዋል።
  1. ሌላው የአዲስ ኪዳን ቃል የወንድማማችነት ፍቅርን ወይም ጓደኛን ወይም ቤተ ሰብን ማፍቀርን የሚመለከተው ነው።
  • ይህ ቃል የሚያመለክተው በጓደኛሞች ወይም በዘመዳሞች መካከል ያለውን ተፈጥሮአዊና ሰብዓዊ ፍቅርን ነው።
  • “በግብዣም በከበሬታ ቦታ መቀመጥ ያፈቅራሉ (ይወዳሉ)” በሚለው ዐውድ ውስጥም ጥቅም ላይ ውሏል። ይህም ማለት ያንን የማድረግ ከፍ ያለ ፍላጎት ወይም ምኞት አላቸው ማለት ነው።
  1. “ፍቅር” የሚለው ቃል በወንድና በሴት መካከል ያለውን መሳሳብና ማደድንም ያመለክታል። 4. “ያዕቆብን ወደድሁ (አፈቀርሁ) ኤሳውን ግን ጠላሁ” በሚለው አነጋገር ውስጥ፣ “ወደድሁ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ያዕቆብ ከእርሱ ጋር የኪዳን ግንኙነት እንዲኖረው እግዚአብሔር መምረጡን ነው። ስለዚህ እዚህ ላይ ይህ ቃል፣ “መረጥሁ” ተብሎ መተርጎም ይችላል ማለት ነው። ምንም እንኳ ኤሳውም በእግዚአብሔር ቢበክም፣ ከእርሱ ጋር ኪዳን የማድረግን መብት አላገኘም። “ጠላሁ” የሚለውም ቃል፣ “አልፈለግሁትም” ወይም፣ “አልመረጥሁም” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።