1.3 KiB
1.3 KiB
የእግዚአብሔር መንግሥት፣ መንግሥተ ሰማይ
“የእግዚአብሔር መንግሥት” እና፣ “መንግሥተ ሰማይ” የሚሉት ሁለቱም የሚያመለክቱት በሕዝቡና በፍጥረት ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያለውን አገዛዝ ነው።
- ስሙን በቀጥታ ላለ መጥራት ብዙ ጊዜ አይሁድ፣ “ሰማይ” የሚለውን ቃል የሚጠቀምበት እግዚአብሔርን ለማመልከት ነው።
- አዲስ ኪዳን ውስጥ ከማቴዎስ ወንጌል እንደምንመለከተው “የእግዚአብሔር መንግሥትን” – “መንግሥተ ሰማይ” በማለት ጠርቶታል፤ ይህን ያደረገው እየጻፈ የነበረው በዋነኛነት ለአይሁድ ስለሆነ ይሆናል።
- የእግዚአብሔር መንግሥት የቁሳዊው ዓለም ገዢ እንደ ሆነ ሁሉ በመንፈሳዊ ደረጃም እግዚአብሔር ሕዝቡን እየገዛ እንደ ሆነ ያመለክታል።
- በጽድቅ እንዲገዛ እግዚአብሔር መሲሑን እንደሚልክ ብሉይ ኪዳን ይናገራል። የእግዚአብሔር ልጅ መሲሑ ኢየሱስ በእግዚአብሔር መንግሥት ለዘላለም ይገዛል።