931 B
931 B
ተዋጊ፣ ወታደር
ሁለቱም ሰራዊት ውስጥ ሆኖ መዋጋትን የሚያመለክቱ በመሆናቸው፣ “ተዋጊ” እና፣ “ወታደር” ትርጕማቸው ተመሳሳይ ነው። ያም ሆኖ ግን፣ መጠነኛ ልዩነትም አላቸው።
- ብዙ ጊዜ፣ “ተዋጊ” የሚለው በጦር ሜዳ ልምድና ድፍረት ያለውን ሰው የሚያመለክት አጠቃላይና ሰፋ ያለ ቃል ነው።
- በምሳሌያዊ አነጋገር ያህዌ ራሱ፣ “ተዋጊ” እንደ ሆነ ተነግሯል።
- “ወታደር” በጣም ግልጽ በሆነ ሁኔታ በአንድ ሰራዊት ውስጥ ወይም ዐውደ ውጊያ ውስጥ የሚዋጋ ሰው ነው።
- በትርጕምና በአጠቃቀም የተለየ ትርጕም ያላቸው ሁለት ቃላት ሊኖር መቻላቸውን ተርጓሚው ልብ ማድረግ አለበት።