am_tw/bible/other/vain.md

9 lines
1.1 KiB
Markdown

# ከንቱ፣ ከንቱነት
“ከንቱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ምንም ጥቅም ወይም ዓላማ የሌለውን ነገር ነው። ከንቱ ነገሮች ባዶና እርባነ ቢስ ናቸው።
* “ከንቱ” እርባና ቢስ ወይም ባዶ ማለት ነው። ትዕቢትና እብሪትን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።
* በእውነት መጸለይ እንጂ፣ “ከንቱ ቃላት መደጋገም” እንደሌለባቸው ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ነግሮአቸዋል፤ እንዲህ ያለው ቃላትን መደጋገም ብቻውን ትርጕም የሌለው መሆኑን ለማመልከት ነ።ው
* ብሉይ ኪዳን ውስጥ ጣዖቶች ማዳን መታደግ የማይችሉ ከንቱዎች ተብለዋል። ጥቅመ ቢስና እርባና ቢስ ናቸው።
* አንድ ነገር “ከንቱ” ሆኖ ከተሠራ ከእርሱ መልካም ውጤት ሊገኝ አይችልም። ጥረት ወይም ተግባር ምንም ማከናወን አይችልም።