939 B
939 B
ችግር፣ መከራ፣ ሁከት
“ችግር” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በጣም አዳጋችና አስጨናቂ የሕይወት ልምምድን ነው። “ሁከት” ከአንዳች ንገር የተነሣ መረበሽ ወይም መጨነቅ ማለት ነው።
- ችግር ሲባል ሰውን የሚጎዳ ማንኛውም አካላዊ፣ ስሜታዊ ወይም መንፈሳዊ ሁከት ሊሆን ይችላል።
- ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው የተለያዩ ችግሮች በእምነታቸው እንዲያድጉና እንዲጠነክሩ ለመርዳት እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸው የመከራና የፈተና ጊዜዎች ናቸው።
- ዐመፀኛ በሆኑትና እግዚአብሔርን ችላ በሚሉ ሕዝቦች ላይ የሚመጣውን ፍርድ ለማመልከት ብሉይ ኪዳን፣ “መከራ” በሚለው ቃል ይጠቀማል።