856 B
856 B
ግብር
ግብር ከለላ ለማግኘትና በሕዝቦቻቸው መካከል መልካም ግንኙነት እንዲኖር አንድ መንግሥት ወይም ገዢ ለሌላው የሚያቀርበው ስጦታ ነው።
- ግብር አንድ ገዢ ወይም መንግሥት ከሕዝቡ የሚሰበስበው ገንዘብ ወይም ዋጋ ያለው ሌላ ነገር ሊሆን ይችላል።
- በጥንት ዘመን ጕዞ ላይ ያሉ ንጉሦች ወይም ገዦች ጥበቃና ከለላ እንዲደረግላቸው ለሚያልፉበት አካባቢ ንጉሥ ወይም ገዢ ግብር ይከፍሉ ነበር።
- ብዙውን ጊዜ ከገንዘብ ሌላ ምግብ፣ ቅመማ ቅመም፣ ውድ ልብሶች፣ እና ወርቅን የመሳሰሉ የከበሩ ድንጋዮችን ግብር ማቅረብ የተለመደ ነበር።