894 B
894 B
መከራ
“መከራ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው መከራና ጭንቀት ያለበት አዳጋች ጊዜን ነው።
- እየኖሩ ያሉት የኢየሱስን ትምህርት የሚቃወም ዓለም ውስጥ በመሆኑ ክርስቲያኖች በስደትና ማንኛውም ዐይነት መከራ ባለበት ሁኔታ ውስጥ እንደሚያልፉ አዲስ ኪዳን ይናገራል።
- ከኢየሱስ ዳግም መምጣት በፊት እግዚአብሔር ለተወሰኑ ዓመታት ቁጣውን በምድር ላይ እንደሚያወርድ ሲያመለክት መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ታላቁ መከራ” በሚል ቃል ይጠቀማል።
- “መከራ” የሚለው ቃል፣ “ታላቅ የመከራ ጊዜ” ወይም፣ “ከባድ ጭንቀት” ወይም፣ “ጽኑ ስደት” በማለት መተርጎም ይቻላል።