832 B
832 B
መንቀጥቀጥ
“መንቀጥቀጥ” ከፍርሃት ወይም ከከባድ ጭንቀት የተነሣ መናወጥ ወይም፣ መንዘፍዘፍ ማለት ነው።
- “በጣም መፍራት” ማለትም ይሆናል።
- አንዳንዴ፣ “መንቀጥቀጥ” መሬቱን የሚያናውጥ ታላቅ ድምፅንም ያመለክታል።
- በእግዚአብሔር ፊት ምድር እንደምትንቀጠቀጥ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይህም ከፍርሃት የተነሣ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ይንቀጠቀጣሉ ወይም ምድር ሯሷ ትንቀጠቀጣለች ማለት ነው።
- እንደ ዐውዱ አገባብ “መፍራት” ወይም፣ “እግዚአብሔርን መፍራት” ወይም፣ “መራድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።