am_tw/bible/other/time.md

10 lines
1.2 KiB
Markdown

# ጊዜ
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ጊዜ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የተወሰኑ ነገሮች የተፈጸሙበትን ወቅት ወይም ዘመን ለማመልከት ነው። “ዕድም” ወይም፣ “ዘመን” ወይም “ወቅት” ጋር የሚመሳሰል ትርጕም አለው።
* ይህ ደቂቃዎች፣ ሰዓቶች፣ ቀኖች ወይም ወሮች ከሚለካበት መለኪያ የተለየ ትርጕም አለው።
* ትንቢተ ዳንኤልና የዮሐንስ ራእይ በምድር ላይ ታላቅ መከራ የሚመጣበት፣ “ጊዜ” መኖሩን አመልከተዋል።
* “ዘመን (ጊዜ)፣ ዘመናትና የዘመን እኩሌታ” የሚለው ሐረግ ውስጥ “ዘመን፣ ጊዜ” የሚያመለክተው አንድ፣ “ዓመትን” ነው። ይህ ሐረግ በዘመን ፍጻሜ ላይ ለሦስት ዓመት ተኩል የሚሆነውን ታላቅ መከራ ያመለክታል።
* “ሁለተኛ ጊዜ” ወይም፣ “ብዙ ጊዜ” የተሰኙት ሐረጎች አንድ ነገር የሆነበትን ድርጊት ቁጥር ያመለክታሉ።
* “በጊዜው” ማለት ሳይዘገዩ በሚጠበቀው ጊዜ መድረስ ማለት ነው።