am_tw/bible/other/thief.md

1.5 KiB

ሌባ፣ ሌቦች፣ ወንበዴ

“ሌባ” ወይም፣ “ወንበዴ” ገንዘብ ወይም ንብረት ከሌሎች የሚሰርቅ ሰው ነው። በብዙ ቁጥር ሲሆን፣ “ሌቦች” ይሆናል።

  • አብዛኛውን ጊዜ ሌቦች አንድን ነገር ሳይታሰብ ለመውሰድ በማድባት ምቹ ጊዜ ይጠብቃሉ። ብዙውን ጊዜ የሚያደርጉት እንዳይታይ ጨለማን ተገን ያደርጋሉ።
  • አንዳንዴ “ወንበዴ” የሚለው ቃል ሌሎችን የሚጎዳ ሰው የሚል ትርጕም ይኖረዋል። ከኢየሱስ ጋር የተሰቀሉት ሰዎች “ወንበዴዎች” ወይም፣ “ወንጀለኞች” ተብለዋል።
  • ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ አዲስ ኪዳን ሰይጣንን ለመሰቅ፣ ለመግድልና ለማጥፋት የሚመጣ ሌባ ብሎታል። ይህም ማለት የሰይጣን ዕቅድ ሰዎች ለእግዚአብሔር መታዘዝ እንዲያቆሙ ማድረግና እግዚአብሔር ያዘጋጀላቸውን መልካም ነገር እንዳይቀበሉ ከእነርሱ መስረቅ ነው ማለት ነው።
  • ሌባ ስዎች ባልጠበቁት ጊዜ እንደሚመጣ፣ ኢየሱስም ሰዎች ባልጠበቁት ጊዜ ይመጣል። እርሱ የሚመጣው በድንገትና ሳይታሰብ ስለሆነ የእርሱን ተመልሶ መምጣት ዘወትር እንዲጠባበቁ ኢየሱስ ለተከታዮቹ ተናግሮአል።