1.1 KiB
1.1 KiB
አሥረኛ፣ አሥራት
“አሥረኛ” ወይም፣ “አሥራት” የተሰኙት ቃሎች የአንድን ሰው ገንዘብ፣ እህል፣ የቤት እንስሳት ወይም ሌሎች ንብረቶች አንድ አሥረኛ ክፍል ያመለክታል።
- በብሉይ ኪዳን ዘመን ለእርሱ ምስጋና እንዲሆን ካላቸው ነገር ሁሉ አንድ አሥረኛውን እንዲሰጡ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል።
- ይህ ስጦታ በካህንነትና መገናኛ ድንኳኑን ወይም ቤተ መቅደሱን በመጠበቅ እስራኤላውያንን ያገለግሉ ለነበሩ ሌዋውያን መደጎሚያ ይውላል።
- አዲስ ኪዳን ለእግዚአብሔር አሥራት እንዲሰጥ አያዝም፤ ይሁን እንጂ ክርስቲያናዊ አገልግሎትንና ድኾችን መርጃ እንዲሆን በልግስናና በቸርነት መስጠትን አጽንዖት ይሰጣል።
- ይህ፣ “አንድ አሥረኛ” ወይም፣ “ከአሥር አንድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።