ምርኩዝ(በትር)
ምርኩዝ ሰዎች ሲራመዱ የሚጠቀሙበት ከእንጨት ወይም ከብረት የተሠራ ከዘራ ወይም በትር ነው
- ያዕቆብ ባረጀ ጊዜ ለመራመድ የሚረዳው ምርኩዝ ይይዝ ነበር
- ኅይሉን ለፈርዖን ለማሳየት እግዚአብሔር የሙሴን በትር እባብ አደረገ
- በጎቻቸውን ለመምራት ወይም ሲወድቁ ለማንሣትና ርቀው ሲሄዱ ለመመለስ እረኞች በምርኩዝ ይጠቀማሉ። ምርኩዝ ጫፉ ቆልመም ያለ በመሆኑ ቀጥ ካለውና በጎቹን ለማጥቃት የሚመጣ አውሬ ከሚያባርርበት የእረኛ በትር የተለየ ነው