am_tw/bible/other/rod.md

11 lines
1.5 KiB
Markdown

# በትር
በትር ቀጭን፣ ጠንካራና በተለያየ መንገድ ጥቅም ላይ የሚውል ከዘራ መሰል ነገር ነው። ምናልባትም በትንሹ አንድ ሜትር ያህል ሊረዝም ይችላል።
* የእንጨት በትር እረኛው በጎችን ከአውሬዎች ለመጠበቅ ይጠቀምበታል። ርቆ የሄደን በግ ወደ መንገድም ለመመለስ ያገለግላል።
* መዝሙር 23 ላይ ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔርን ምሪትን ለመግለጥ፣ እንደ ተለዋጭ ዘይቤ፣ “በትር” እና፣ “ምርኩዝ” በተሰኙ ቃሎች ይጠቀማል።
* የእረኛው በትር በበታቹ እንዲያልፉ በማድረግ በጎቹን ለመቁጠር ይጠቅማል። “በበትር ሥር ማለፍ” የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር በሥልጣን ሥር መሆንን ያመለክታል።
* “የብረት በትር” የሚለው ሌላው ተለዋጭ ዘይቤ በእርሱ ላይ የሚያምጹትንና ክፉ የሚያደርጉትን እግዚአብሔር እንደሚቀጣ ያመለክታል።
* በጥንት ዘመን ከብረት፣ ከእንጨት ወይም ከሌላ ነገር የተሠራ መለኪያ በትር ሕንፃንና የተለያየ ነገርን ለመለካት ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
* በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት፣ የእንጨት በትር ልጅን ሥርዓት ለማስያዝ ጥቅም ላይ ይውል ነበር።