am_tw/bible/other/return.md

10 lines
1.1 KiB
Markdown

# መመለስ
“መመለስ” ወደ ኋላ መመለስ፣ ወይም አንድን ነገር መልሶ መስጠት ማለት ነው።
* ወደ አንድ ነገር መመለስ፣ እንደ ገና ያንን ነገር ማድረግ መጀመር ማለት ነው።
* እስራኤላውያን ወደ ጣዖት አምልኮአቸው ሲመለሱ፣ እንደ ገና እነርሱ ማምለክ ጀምረዋል ማለት ነው።
* ወደ እግዚአብሔር ተመልሰዋል ከተባለ ንስሐ ገብተዋል፤ እንደ ገና ያህዌን ማምለክ መጀመራቸውን ያመለክታል።
* ከአንድ ሰው የወሰድነውን ወይም የተቀበለውን ርስት ወይም ንብረት የምንመልስ ከሆነ ያንን ርስትና ንብረት ለመጀመሪያው ባለቤቱ መልሰን እንሰጣለን ማለት ነው።
* “መመለስ” የሚለውን፣ “ወደ ኋላ መሄድ” ወይም፣ “መልሶ መስጠት” ወይም፣ “ያንኑ ማድረግ መጀመር” በማለት መተርጎም ይቻላል።