am_tw/bible/other/reed.md

1.2 KiB
Raw Permalink Blame History

መጠጊያ

“መጠጊያ” የሚለው ቃል ዋስትናና ጥበቃ ያለበትን ቦታን ወይም ሁኔታን ያመለክታል። “መጠቢያ” ከዝናብ ወይም ከአደጋ የሚከልል ነገር ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ሕዝቡ ጥበቃ፣ ጥንቃቄና ሰላም የሚያገኙበት መጠጊያ እንደ ሆነ ተነግሯል።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “የመጠጊያ፣ የመማጸኛ ከተማ የሚለው ቃል ሳያስበው ሰው የገደለ ሰው፣ የበቀል ጥቃት እንዳይደርስበት በፍጥነት በመሄድ የሚጠለልባቸውን ከተሞች ያመለክታል።
  • ብዙውን ጊዜ ለሰዎች ወይም ለእንስሳት ከለላ የሚሆን ሕንፃ ወይም ጣራ፣ “መጠጊያ” ተብሎ ይጠራል።
  • እንግዶቹ ከእርሱ ቤት ጣራ በታች “የተጠጉ” መሆናቸውን ሎጥ ከተናገረው መመልከት እንደሚቻለው፣ “መጠጊያ” “መከለያ” ማለትም ይሆናል። ሎጥ እንዲህ ያለው በእርሱ ቤት እስካሉ ድረስ ምንም ጉዳት እንደማይደርስባቸው ለማመልከት ነው።