am_tw/bible/other/prosper.md

1.8 KiB

መበልጸግ/መከናወን፣ ብልጽግና፣ የበለጸገ

“መበልጸግ” አንድ ሰው ወይም ሕዝብ በሕይወታቸው ሲከናወኑ ወይም የተሳካላቸው ሲሆኑ ማለት ነው። ይህ መከናወን ቁሳዊ ወይም መንፈሳዊ ሊሆን ይችላል። “ብልጽግና” ሀብታምና ደኅና የመሆን ሁኔታ ነው።

  • ሰዎች በሕወትና በጤንነት ወይም በሀብት የተሳካላቸው ሲሆኑ በለጸገ ይባላል።
  • ብዙውን ጊዜ “ብልጽግና” የሚለው ቃል ገንዘብና ንብረትን በተመለከተ የተሳካላቸው መሆኑን ያመለክታል።
  • በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት፣ “የበለጸገ” የሚለው ቃል በመልካም ጤንነትና በልጆች መባረክንም ይጨምራል።
  • “የበለጸገ” ከተማ ወይም አገር ብዙ ሕዝብ፣ የተትረፈረፈ ምግብና፣ ብዙ ገንዘብ የሚያስገኝ ንግድና ሌሎች ተግባሮች የተሳካለት ማለት ነው።
  • አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ትምህርቶች ሲታዘዝ በመንፈሳዊ ሕይወት እንደሚበለጽግ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። በደስታና ሰላምም ይባረካል። እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሌም የተትረፈረፈ ቁሳዊ ሀብት ላይሰጣቸው ይችላል፤ ይሁን እንጂ፣ የእርሱን መንገድ ከተከተሉ ሁሌም በመንፈሳዊ ሕይወት ይባርካቸዋል።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “መበልጸግ” የሚለው ቃል፣ “መንፈሳዊ ስኬት” ወይም፣ “በእግዚአብሔር መባረክ” ወይም፣ “መልካም ነገሮችን መለማመድ” ወይም፣ “መሳካት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።