946 B
946 B
መሾም (ዕውቅና መስጠት)
መሾም ሲባል ወግ ባለው ሁኔታ ለተለየ ተግባር ወይም ድርሻ አንድን ሰው መለየት ማለት ነው። በዐዋጅ ደረጃ ሕግን ወይም ደንብን ማሳወቅ ማለትም ይሆናል።
- “መሾም” የሚለው ቃል ካህን፣ አገልጋይ ወይም የሃይማኖት መምህር እንዲሆን ወግ ባለው መልኩ አንድን ሰው መርጦ ለዚሁ ተግባር መለየት ማለት ነው።
- ካህናት እንዲሆኑ እግዚአብሔር አሮንና ልጆቹን ሾሟቸው ነበር።
- ሃይማኖታዊ በዓልን ወይም ኪዳን መመሥርት ማለትም ይሆናል።
- “መሾም” እንደ አውዱ ሁኔታ፣ “መለየት” ወይም፣ “ማዘዝ” ወይም፣ “ደንብ ማውጣት” ወይም፣ “መመሥረት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።