1.0 KiB
1.0 KiB
የወይራ ፍሬ
የወይራ ፍሬ ከወይራ ዛፍ የሚገኝ ትንሽ ሾጣጣ ቅርጽ ያለው ፍሬ ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ የሚገኘው በሜድትራኒያን ባሕር አካባቢዎች ነው።
- የወይራ ዛፍ ሁልጊዜ ለምልሞ የሚታይና ነጫጭ አበቦች ያሉት ቁጥቋጦ ነው። ጥሩ ሆኖ የሚያድገው ሞቃት የአየር ጸባይ ባለበት ቦታ ሲሆን፣ ጥቂት ውሃ ካገኘ እንደለመለመ የመዝለቅ ባሕርይ አለው።
- የወይራ ፍሬ መልኩ አረንጓዴ ቢሆንም፣ እየበሰለ ሲሄድ ይጠቁራል። የወይራ ፍሬ ለመብል ይሆናል፤ ዘይትም ይወጣዋል።
- የወይራ ዘይት ለምግብ ብቻ ሳይሆን፣ በሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት መብራት በመሆንም ያገለግላል።
- መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የወይራ ዛፍ ምሳሌያዊ በሆነ አነጋገር ሰዎችንም ያመለክታል።