am_tw/bible/other/oil.md

8 lines
968 B
Markdown

# ዘይት
ዘይት ከአንዳንድ ተክሎች ወይም ፍሬዎች ሊገኝ የሚችል ወፈር ያለ ፈሳሽ ነገር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን አብዛኛውን ጊዜ ዘይት የሚገኘው ከወይራ ፍሬዎች ነው።
* የወይራ ዛፍ ለምግብ ማጣፈጫ፣ ለቅባት፣ ለመሥዋዕት፣ ለመብራትና ለመድኃኒትነት ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
* በጥንት ዘመን የወይራ ዛፍ ትልቅ ዋጋ ነበረው፤ የዘይት ባለቤት መሆን የሀብታምነት መገለጫ ተደርጎ ይታሰብ ነበር።
* በዚህ ቃል ስንጠቀም ለምግብ የሚሆነው ዘይት እንጂ፣ ለሞተር የሚሆን ዘይትን የሚያመለክት እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብን። አንዳንድ ቋንቋዎች ለተለያዩ የዘይት ዓይነቶች የተለያዩ ቃሎች አሏቸው።