813 B
813 B
ወርካ
ወርካ ረጅም፣ ትልቅ ግንድና ጥላ የሚሆኑ ሰፋፊ ቅርንጫፎች ያሉት ዛፍ ነው።
- የወርካ ዛፎች መርከቦችንና የእርሻ ሞፈሮችን፣ የበሬ ቀንበሮችንና ለሽማግሌዎች የሚሆኑ ምርኩዞችን ለመሥራት የሚያገለግሉ ጠንካራ እንጨቶች ያሉዋቸው ዛፎች ናቸው።
- የወርካ ዛፍ ዘር፣ “ፍሬ” ይባላል።
- የአንዳንድ ወርካ ዛፍ ቅርንጫፎች 6 ሜትር ገደማ ያህል ስፋት አሏቸው።
- ወርካ የረጅም ዕድሜ ምሳሌ ሲሆን፣ ሌሎች መንፈሳዊ ትርጕሞችም አሉት። አብዛኛውን ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ቅዱስ ከሚባሉ ቦታዎች ጋር ይያያዛል።