1.2 KiB
1.2 KiB
ጎረቤት
አብዛኛውን ጊዜ ጎረቤት የሚባለው በአካባቢው የሚኖር ሰው ነው። ይበልጥ አጠቃላይ በሆነ መልኩ፣ በምትኖሩበት ማኅበረ ሰብ ወይም የሰዎች ስብስብ ውስጥ የሚኖር ሰውን ያመለክታል።
- “ጎረቤት” የሚለው አንዱ ትርጕም፣ እናንተ በምትኖሩበት ማኅበረ ሰብ ውስጥ የሚኖር በመሆኑ ከለላ የምትሆኑትና ደግ የምትሆኑለት ሰው ማለት ነው።
- ስለ መልካሙ ሳምራዊ አዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ በተናገረው ምሳሌ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ፣ “ጎረቤት” የሚለውን ቃል የተጠቀመበት ሌላው ቀርቶ ጠላት የሚባለው እንኳ ሳይቀር የሰው ልጅን ሁሉ በሚያካትት ሰፋ ባለ ሁኔታ ነው።
- የአሥሩ ትእዛዞች የመጨረሻዎቹ ስድስቱ ሌሎች ሰዎችን ማለትም ጎረቤቶችን መውደድ ላይ ያተኵራሉ።
- የሚቻል ከሆነ ይህን ቃል በቃል ለመረርጎም “አጠገብህ የሚኖር ሰው” የሚል ትርጕም ባለው ቃል ወይም ሐረግ መጠቀሙ የተሻለ ነው።