1.1 KiB
1.1 KiB
ቅርጽ ማውጫ
ቅርጽ ማውጫ የሚባለው ከወርቅ፣ ከብርና ከሌሎች ፈሳሽ መሆን ከሚችሉ ነገሮች አንዳንድ ነገሮችን ለመሥራት የቅርጽ ማውጫውን ይዘው እንዲወጡ ለማድረግ ከእንጨት ቁራጭ፣ ከብረት ወይም ከሸክላ ተፈልፍሎ የሚሠራ ነገር ነው።
- ቅርጽ ማውጫዎች ሌሎች ነገሮችንም ጨምሮ ጌጣጌጦችን፣ ሳህኖችንና የመመገቢያ ዕቃዎችን ለመሥራት ያገለግላሉ።
- መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅርጽ ማውጫዎች እንደ ጣዖት ያሉትን ሐውልቶችና የሐሰኛ አማልክት ማምለኪያ ነገሮችን ከመሥራት ጋር በተያያዘ ነው በዋናነት የተጠቀሱት።
- ቅርጽ ማውጫው ውስጥ ማፍሰስ እንዲቻል በመጀመሪያ ወርቁ ወይም ብሩ በእሳት መቅለጥ አለበት።
- አንድን ነገር መቅረጽ በመቅረጫው ወይም በእጅ በማበጀት ያ ነገር የተወሰን ቅርጽ ወይም ምስል ይዞ እንዲወጣ ማድረግ ነው።