am_tw/bible/other/meek.md

9 lines
778 B
Markdown

# የዋህ፣ የዋህነት
“የዋህ” የሚለው ቃል ጨዋ፣ እሺ ባይና መከራን በትዕግሥት የሚቀበልን ሰው ያመለክታል። መናደድ ኀይል መጠቀም ተገቢ መስሎ ቢታይ እንኳ ጨዋ ሆኖ ለመገኘት የዋህነት ታላቅ ችሎታ ነው።
* ብዙ ጊዜ የዋህነት ከትሕትና ጋር ይያያዛል።
* እርሱ የዋህና በልቡም ትሑት እንደ ሆነ ኢየሱስ ተናግሮአል።
* ይህ ቃል፣ “ጨዋ” ወይም፣ “ረጋ ያለ” ወይም፣ “ገር” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
* “የዋህነት” የሚለውም ቃል፣ “ጨዋነት” ወይም፣ “ትሕትና” ተብሎ መተርጎም ይችላል።